AYNEMA WEDAJESH

አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ
ጥርሴማ ወዳጅሽ አላንቺ አልስቅ አለ
ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ ያደረ
እህል በልቶ ያደረ
አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ
ጥርሴማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ
ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ ያደረ
እህል በልቶ ያደረ
 
የአባይ ዳሩ ዳሩ ያበቅላል ጠምበል
የአባይ ዳሩ ዳሩ ያበቅላል ጠምበል
ዋጥ ላርጋትና አላየሁም ልበል
ዋጥ ላርጋትና አላየሁም ልበል
እኔ አይኔን አሞኛል ወይ አልሞት አልድን
እኔ አይኔን አሞኛል ወይ አልሞት አልድን
እሷንም ጥሎባት እንደኔ ትሁን
እሷንም ጥሎባት እንደኔ ትሁን
አይሽ አይሽና ሳቅ ይከጅለኛል
አይሽ አይሽና ሳቅ ይከጅለኛል
እኔ ያሳለፍኩት ባንቺ ይታየኛል
እኔ ያሳለፍኩት ባንቺ ይታየኛል

አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ
ጥርሴማ ወዳጅሽ አላንቺ አልስቅ አለ
ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ ያደረ
እህል በልቶ ያደረ
አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ
ጥርሴማ ወዳጅሽ አላንቺ አልስቅ አለ
ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ ያደረ
እህል በልቶ ያደረ

ባይንሽ ጉድፍ ገባ ሁሉን አይ’ ብለሽ
ባይንሽ ጉድፍ ገባ ሁሉን አይ’ ብለሽ
ሳያምሽ አይቀርም ሳይቆረቁርሽ
ሳያምሽ አይቀርም ሳይቆረቁርሽ
ምነው ኩላሊቴን ምነው የደሜን ስር
ምነው ኩላሊቴን ምነው የደሜን ስር
የዋለ ያደረ ጥል ያለን ይመስል
የዋለ ያደረ ጥል ያለን ይመስል
በአዛኚቱ ማርያም በወለላዪቱ
በአዛኚቱ ማርያም በወለላዪቱ
የታመመ ሳይድን አይንጋ ሌሊቱ
የታመመ ሳይድን አይንጋ ሌሊቱ
አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ

ጥርሴማ ወዳጅሽ አላንቺ አልስቅ አለ
ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ ያደረ
እህል በልቶ ያደረ
እስኪ ሰው ጥሩልኝ እኔ ድምፅ የለኝም
እስኪ ሰው ጥሩልኝ እኔ ድምፅ የለኝም
እ’ርቆ ከሄደ ወዳጅ አይገኝም
እ’ርቆ ከሄደ ወዳጅ አይገኝም
ትላንትም አልበላሁ ዛሬም ፆሜን አደርኩ
ትላንትም አልበላሁ ዛሬም ፆሜን አደርኩ
ሰውም አልጠየቀኝ እኔም አልተናገርኩ
ሰውም አልጠየቀኝ እኔም አልተናገርኩ
ቁና ጥሬ ልብላ አመት ልመንን
ቁና ጥሬ ልብላ አመት ልመንን
እሷን በሱባዔ አገኝ እንደሆን
እሷን በሱባዔ አገኝ እንደሆን
እኔ ቤት አልሄድም እሷን እፈራለሁ
እኔ ቤቷ አልሄድም እሷን እፈራለሁ
ዓይኗ ሰው ይወጋል ሲሉ ሰምቻለሁ
ዓይኗ ሰው ይወጋል ሲሉ ሰምቻለሁ

አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ
ጥርሴማ ወዳጅሽ አላንቺ አልስቅ አለ
ሆዴ ነው ጠላትሽ እህል በልቶ ያደረ
እህል በልቶ ያደረ
አይኔማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ
ጥርሴማ ወዳጅሽ አላንቺ አላይ አለ
Scroll to Top