EYANGELATAGN NEW

እያንገላታኝ ነው
መሬት የማይነካኝ ባየር ላይ ነጣሪሽቅርቅር አማላይ ነገር አሳማሪከኔ በላይ ማነው ብዬ ምፎክር
ነበርኩ እኔ ላገር ማስቸግር
ወይ ጊዜ ወይ እጣ ክፉ ቢገጥመኝፍቅር ጠልፎ ጥሎ ከቤት አዋለኝትቢቴን አንጥፎ ከመሬት የጣለው
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው
ጠዋት እስከ ማታ እያንገላታኝ ነውሆነሽ ሁሉም ቦታ እያንገላታኝ ነውእኔስ ምን ላድርግሽ ውዴ የኔ ገላ
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው
የኔ እንዲያ መገንፈል ሀገር ማጥለቅለቁአውቀው አሳለፉኝ ቀን እየጠበቁበጉልበት ላይ ጉልበት ሲመጣ ድንገትያስጨንቃል ያስብላል ወዴት

በሰከነ መንፈስ በረጋው ቃልሽስታነጋግሪኝ ኩራቴን ጥሰሽስንት እርቀት ሄደሽ ነካካሽኝ ይኸውፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው

ጠዋት እስከ ማታ እያንገላታኝ ነውሆነሽ ሁሉም ቦታ እያንገላታኝ ነው
እኔስ ምን ላድርግሽ ውዴ የኔ ገላፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው

አቅሜን ያጣሁ ሰው ነኝ አቅሜን አጣሁኝ ዛሬአንገቴን እያስደፋኝ ባንቺ ሰው መቸገሬአንቺ እንደኔ አይደለሽ እንደኔማ አይደለሽድረሽልኝ በሞቴ ነይ ባክሽ ቶሎ ብለሽ

መዳን ነው ይሉኛል መዳን ነው ይሉኛል ሁሉምፍቅር የነካው ሰው ፍቅር ነው ሚወጣው ቃሉአንቺን ምክንያት አርጎ ፍቅርማ እኔን ካዳነሁሉንም ልቀበል ልቤም ይሁን የታመነ

ጠዋት እስከ ማታ እያንገላታኝ ነውሆነሽ ሁሉም ቦታ እያንገላታኝ ነውእኔስ ምን ላድርግሽ ውዴ የኔ ገላፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው
 
 
Scroll to Top