Eyut

ፍቅሩ አስክሮኝ አንገዳግዶኝ

ድጋፌ ስለው አስደግፎኝ

እንዳልሄደ እንዳልጣለ ያኔ ትቶኝ

እዩት ሲለምነኝ 4*

በሱ የተነሳ ተበላሽቶ ስሜ

ፍቅሩ አመንምኖኝ አይሆኑ ታምሜ

ገና ሳላገግም በሽታዬ ሳይድን ከቁስሌ ሳልጠና

አሁን ምን ሊረባኝ የሱ መለማመጥ ድጋሚ ልመና

እኔ እንኳን ብቀርበው ሰው ይታዘበኛል

የሰራኝን ስራ ሀገር ያውቅልኛል

ተከፍሎ የማያልቅ ሆኖብኝ እዳዬዬዬ

ጨርቄን መጣል ቀርቶኝ ባልበላሁት እዳ ማበድ

ውሀ የሚያጣጣኝ ጓደኛ አጥቼ ዘመድ

የሴት ክብሬን ትቼ ለምኜው ለምኜው ጉድ ሰርቶኝ

እዩት እዩት እዩት ዛሬ ሲለምነኝ

እዩት ሲለምነኝ 4*

እዩልኝ ስሙልኝ የሱን መብከንከን

ስለምነው ሄዶ አሁን ሲለምን

እኔ ቆርጦልኛል ባይሆን ሰው ካገኘ ለፍቅሩ ምሽግ

ባጣ ቆዪ ሲላት እሺ የምትለው ሌላ ይፈልግ

እኔ እንኳን ብቀርበው ሰው ይታዘበኛል

የሰራኝን ስራ ሀገር ያውቅልኛል

ተከፍሎ የማያልቅ ሆኖብኝ እዳዬዬዬ

ጨርቄን መጣል ቀርቶኝ ባልበላሁት እዳ ማበድ

ውሀ የሚያጣጣኝ ጓደኛ አጥቼ ዘመድ

የሴት ክብሬን ትቼ ለምኜው ለምኜው ጉድ ሰርቶኝ

እዩት እዩት እዩት ሲለምነኝ

እዩት ሲለምነኝ 4*

Scroll to Top