Gelemele

እገሌ አትርፎ እገሌ ከስሯልእገሌ ቀልቶ እገሌ ጠቁሯልስለ ሠው ብቻ ሲሆን ወሬያችንበጣም አስፈራኝ የኛ ፍቅራችንእንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌእንደራሴ ነው ምኖረው ልክ እንደ ዐመሌእንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌስለ ፍቅራችን ስትይ ተይ ገለመሌ
እንቶ ፈንቶና ወሬ ገለመሌተይ አይጠቅመንም ፍቅሬ ገለመሌስለ ሰው ስናወራ ተይ ተይ ፍቅሬየኛን ነገር አደራ ተይ ተይ ፍቅሬእንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌእንደራሴ ነው ምኖረው ልክ እንደ ዐመሌእንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌስለ ፍቅራችን ስትይ ተይ ገለመሌ
እገሌ አልቅሷል አልቅስ አትበይኝእገሌ ስቋል ሳቅ አትበይኝየራሴ እምባ አለኝ የራሴ ሳቅሰው ተከትዬ አልሳቀቅእንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌእንደራሴ ነው ምኖረው ልክ እንደ ዐመሌእንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌስለ ፍቅራችን ስትይ ተይ ገለመሌ
ከሰው ጋ መፎካከር ገለመሌከሰው ጋ መወዳደር ገለመሌእስቲ ስለኛ እናውራ ነይ ነይ ፍቅሬበግልፅ እንመካከር ነይ ነይ ፍቅሬእንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌእንደራሴ ነው ምኖረው ልክ እንደ ዐመሌእንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌስለ ፍቅራችን ስትይ ተይ ገለመሌ
ሰው እንደቤቱ ይኖራል እንጂእንደ ጎረቤትማ መቼም አይበጅለመመሳሰል ከመሰባሰብበስንት ጣዕሙ ፍቅሬ ለብቻ ማሰብእንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌእንደራሴ ነው ምኖረው ልክ እንደ ዐመሌእንደነ እንትና አልኖርም እንደነ እገሌስለ ፍቅራችን ስትይ ተይ ገለመሌ
Scroll to Top