MISIKIR

ምስክር
ምስክር ተደርጎ ይደመጥ ትንፋሼ
ላሳየኝ ፍቅር ይሰማ ምላሼ
እስኪ እማኝ ልሁን ለሀሳብ ደራሼ
እስኪ እማኝ ልሁን ለሀሳብ ደራሼ
እስኪ እማኝ ልሁን ለሀሳብ ደራሼ

የምትወደድ ነሃ
የምትወደድ ነሃ
የምትወደድ ነሃ
የምትወደድ ነሃ
የምትወደድ ነሃ
የፍቅር እህል ውሀ

አምናና ካቻምና አዳማጭ አጥቼ
አላወራም ነበር የሆዴን አውጥቼ
ያለፈው ዝምታ አይኖርም ዘንድሮ
አንተ ሰተኧኛል የልብህን ጆሮ
እመነኝ እመነኝ
እመነኝ ምንጊዜም ያንተው ነኝ
እመነኝ ምንጊዜም ያንተው ነኝ

የሁሉም ስጦታ ገንዘብ እና ንብረት
አይበልጥም ወይ ፍቅር ከዚህ ሁሉ ወረት
እንደው ለጨዋታው እንደው ለነገሩ
ልብ የሚሰጥ ወዳጅ አለ ወይ ባገሩ

እመነኝ
እመነኝ
እመነኝ ምንጊዜም ያንተው ነኝ
እመነኝ ምንጊዜም ያንተው ነኝ

ምስክር ተደርጎ ይደመጥ ትንፋሼ

ላሳየኝ ፍቅር ይሰማ ምላሼ
እስኪ እማኝ ልሁን ለሀሳብ ደራሼ
እስኪ እማኝ ልሁን ለሀሳብ ደራሼ
እስኪ እማኝ ልሁን ለሀሳብ ደራሼ

ሰላሜ ልበልሃ
ደስታዬ ልበልሃ
ኩራቴ ልበልሃ
እምነቴ ልበልሃ
ህይወቴ ልበልሃ
የፍቅር እህል ውሃ


የት ደረሰ ስለው አጥቼው ከሌላ
ሊያኗኑረኝ መቷል መውደድ ባንተ ገላ

ከመንፈስህ ገዳም ገባሁ እንደ መና
ካካልህ አልፌ ከነብስህ ልገናኝ

የት ደረሰ ስለው አጥቼው ከሌላ
ሊያኗኑረኝ መቷል መውደድ ባንተ ገላ
ከመንፈስህ ገዳም ገባሁ እንደ መና
ካካልህ አልፌ ከነብስህ ልገናኝ


እመነኝ እመነኝ
እመነኝ ምንጊዜም ያንተው ነኝ
እመነኝ ምንጊዜም ያንተው ነኝ
ባይኔ እነደው ባይኔ ባይኔ
ባይኔ ፍቅር አየው ባይኔ
ባይኔ ኧረ ባይኔ ባይኔ
ባይኔ መውደድ አየው ባይኔ
ባይኔ ኧረ ባይኔ ባይኔ
ባይኔ ፍቅር አየው ባይኔ
ባይኔ ኧረ ባይኔ ባይኔ
ባይኔ መውደድ አየው ባይኔ
Scroll to Top