አይለምደኝም ዳግም ማሪኝ ውድዬ
አልዋሽሽም እናት በስምሽ ምዬ
ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ
እውነት አለው ልብሽ አዝነሽ ቢከፋሽም
የሰራሁት በደል ላንቺ አይገባሺም
ይቅር በይኝ እንጂ ሌላ ምን እላለው
ፍፁም ነኝ ለማለት አፌስ ምን አፍ አለው
እኔው ነኝ እኔው ነኝ እኔ ነኝ ያበድኩት
ልብ እና እምነትሺን ቃሌን የሰበርኩት
እኔው ነኝ እኔ ነኝ እኔ ነኝ ክፉ ሰው መቀጣት የሚያንሰው
ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ ይቅርታ